Recent Posts

ጊዜን ማባከንን ለማቆም ማደረግ ያለብንን 3 ነገሮች

“ጊዜ የለኝም ወይም ደክሞኛል”  የብዙዎቻችን የምንደጋግመው ሐረግ ነው። በተለይ በተለይ እውቀታችንን ለማዳበር ፣ ሰውነታችንን ለመገንባት፣ መፈሳዊ ሕይወታችንን ለማበልፀግ በአጭሩ ሁለእንተናዊ  ማንነታችንን ለማሻሻል ጥረት ማደረግ ሲጠበቅብን የምንሰጠው ምክንያት ነው። ጊዜ ጨራሽ ተከታታይ  ድራማዎችን ለማየት፣ ቡና እስከ ሶስተኛው ለመጠጣት፣ ወይም የሌሎች ሰዎችን ግላዊ ሕይወት የሚበረብሩ ፎቶ የበዛባቸው መፀሄቶችን ለማገላበጥ ግን በርካታ ሰአታት አሉን። ብዙ ጊዜ ችግራችን ጊዜ […]

ጥሩ ልማዶችን ማዳበር እንዴት እንችላለን?

ጥሩ ልምዶችን ማዳበር ለስኬት አንደኛ እና አሰፈላጊ ነገር መሆኑ የማያጠራጥር ጉዳይ ነው። ጥሩ ልምዶች ውጤታማ ሕይወትን እንደንኖር ፣ ጊዜን በአግባብቡ መጠቀም እንድንችል ፣ ጤናችን እንዲሻሻል፣ ገቢያችን እንዲጨምር፣ ደስተኛ የሆነ ኑሮን መምራት እንደንችል ብሎም ደግሞ መንፈሳዊ ሕይወታችን እንዲበለፀግ ያስችሉናል።  ልምድ ስር ሰደድ ነው። ከአስተዳደጋችን ከልጅነታችን ጀምሮ በውስጣችን የተቀረፀ ነገር ነው። ለምሳሌ በእደሜ የገፉ ሰዎችን ´አንቱ´ በለን […]

ስኬታማ አመትን ማቀድ እንዴት እንችላለን?

ስኬት በዘፈቀደ የሚሆን ነገር ሳይሆን በእቅድ የሚሆን ነገር ነው። ህይወታችንን በተሳካ ሁኔታ ማቀድ የምንፈልግ ከሆነ ይህንን ፅሁፍ አንብበን ተግባር ላይ እናውለው። አመታዊ እቅድን ማውጣት ከአመታት በፊት ከተማርኩ ጀምሮ ወደ ሗላ አላየሁም። አመታዊ ዕቅድን ማውጣት በማስተዋል እንድንኖር ፣ ጊዜን እንዳናባክን ፣ የሚያስፈልጉን ነገሮች ላይ እንድናተኩር እና ያለፈውን አመት በጥሩ ሁኔታ መገምገም እንደንችል ይረዳናል። ትልልቅ ድርጅቶች አመታዊ […]

2020 ያስተማረኝ ነገር

2020 ያስተማረኝ ነገር በህይወቴ በጣም ጠቃሚ ናቸውም ከምላቸው ልምዶች ውስጥ አንዱ ያለፈውን አመት መለስ ብሎ ማየት እና አመቱ ምን አስተምሮኝ አለፈ ብዬ እራሴን መጠየቅ ይገኝበታል። ይህንን የማደርገው አመቱን በጥሩ ሁኔታ መገምገሜ የሚመጣወን አዲስ አመት ለማቀድ ጥሩ መሰረትን ይሰጠኛል በሚል እምነት ነው ።ከዚህ በታች 2020 ካሰተማረኝ ውስጥ ስምንቱን አካፍላችሗለው። እናንተ ምን ተማራችሁ ? ፈቃደኛ ከሆናችሁ አስተያየት […]

የጥበቃ ጊዜን እንዴት ማሳለፍ አለብን?

የተመኘነው እጃችን ሲገባ ብቁ ሆነን መገኘት እንድንችል የጸሎታችን መልስም ፈጥኖ እንዲገለጥ ማስተዋል ያለብን ሶስት ነገሮች! 2. በየቀኑ ወደ ህልማችን የሚያስጠጋንን እርምጃ መውሰድ ። ነገ የፈለግነው ቦታ ላይ እንድንደርስ ዛሬ ማድረግ ያለብን አንድ ነገር ምንድን ነው ብለን ራሳችንን መጠየቅ ወደ ህልማችን የሚያደርሰንን መንገድ አጥርተን እንድናይ ይረዳናል። ጥበቃ እጅን አጣጥፎ ቁጭ ማለት ሳይሆን ህልማችንን እውን ማድረግ የኛ […]

ማንነታችን

እግዚኣብሄር ስለ እኛ ያለው አመለካከት ምን ይመስላል? እኛስ ራሳችንን እንዴት እናያለን? ብዙ ጊዜ ሃሳባችን ከሃሳቡ መንገዳችን ከመንገዱ የራቀ ነው። ታዲያ ምናለባት እግዚኣብሄር እኛን የሚያይበት አይን እኛ እራሳችንን ከምናይበት እጅግ የራቀ ይሆን ወይስ ከሃሳቡ ጋር ተ ሰማምተን እርሱ ያለንን ነን ብለን ህይወትን እንጋፈጣለን? እግዚኣብሄር እኛን ሲያይ ከጨለማ የወጣ በብርሃን የሚመላለስ ፣ የተጠራበትን የሚያውቅ ፣ በድንግዝግዝ ግራ […]

ፍርፋሪ መለመንን የለመደ ቀና ብሎ አያይም

ከንናዊትዋ የእምነት ሴት ግን ምንም እንኳን እንደ ህጉ ፈውስን የመጠየቅ መብት ባይኖራትም በእምነት፣ በድፍረት የልጆች እንጀራ የሆንውን ፈውስን ለመነች። በክርስቶስ ያለን እኛ ግን ፈውስ፣ ሰላም፣ ድል በጠቅላላው ሁለንተናዊ የሆነ ስኬት እድል ፈንታችን ነው። እኔን ጨምሮ ብዙዎቻችን ግን ልመናችን እንደ ልጅ ሳይሆን እንደ እንግዳ ነው። እንጀራውን ሳይሆን ፍርፋሪውን ነው የምንጠይቀው። በፈረንጆቹ አቆጣጠር የአመቱ መገባድጃ እየተቃረበ ነው። […]

ለውጥ ለማምጣት ማድረግ ያለብን አንድ ነገር

የምንፍልገውን ነገር ከማድረግ የሚያስፈልገንን ማድረግ የ10 ደቂቃ ስፖርት ጠዋት ጠዋት ( 5am) መስራት ጀምሬያለው። እንዴት ከባድና አሰልቺ እንደሆነ ልነነግራችሁ አልችልም። 10 ብቻ ደቂቃ ቢሆንም እንኳን ረጅም ሰዓታት እንደሚፈጅ ሆኖ ይሰማኛል። ቀላል የሆኑ በተፈጥሮ ከተሰጡን ስጦታወች ጋር የሚጣጣሙ ነገሮችን ብቻ መስራት ራሳችን ያስለመድን ከሆነ ጥረት እና ትዕግሥት የሚጠይቁ ነገሮችን መስራት በጣም ይከብደናል። ሁል ጊዜ ቀላል ነገሮችን […]

በእግዚአብሔር ቤት የትኛው ልጅ ነን?

በእግዚያብሄር ቤት በየተኛው ልጅ እራሳችንን እንመስላለን? ከእነርሱም ታናሹ ልጅ አባቱን፣ ‘አባቴ ሆይ፤ ከሀብትህ ድርሻዬን ስጠኝ’ አለው፤ ሉቃስ 15:12 ➿➿➿ እርሱ ግን መልሶ አባቱን እንዲህ አለው፤ ‘እነሆ፤ ይህን ያህል ዘመን እንደ ባሪያ አገልግዬሃለሁ፤ ከትእዛዝህም አንዱን እንኳ አላጓደልሁም፤ አንተ ግን ከባልንጀሮቼ ጋር እንድደሰት አንዲት የፍየል ግልገል እንኳ አልሰጠኸኝም፤ ሉቃስ 15:29 🌸 አንደኛው ሰነፍ ነው ስራ አይወደም ሁልጊዜ […]

ያለፈውን አመት ዞር ብለን ስናየው 👀 🔙 2018

ያለፈውን አመት ወደ ሗላ ዞር ብሎ ማየት ወደፊት ጥሩ እቅድ ለማውጣት የሚያስችለን ወሳኝ እርምጃ ነው። ይህንን ለማድረግ የተለያዩ ሰዎች የተለያዩ ጊዜዎችን ይጠቀማሉ። ለምሳሌ ስኬታማ አመራርን በማስተማር የታወቀው ጆን ሲ ማክስዌል በገና እና በ አዲስ አመት መካከል ያሉትን ሳምንታት ለዚህ አላማ ያውላቸዋል። እኔ በበኩሌ የ December ወርን በሙሉ ለዚህ አገልግሎት እጠቀምበታለው ። በፈረንጆች አቆጣጠር ለምትቆጥሩ ሰዎች […]